Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ለ6ኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ህጋዊ እውቅና አግኝተው የሚንቀሳቀሱ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አቋቁመዋል፡፡
የጋራ ምክር ቤት የመሰረቱት የፖለቲካ ፓርቲዎችም ብልፅግና ፓርቲ፣ ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ፣ ለኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ፣ የሀረሪ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት እና እናት ፓርቲ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የምክር ምክር ቤቱ መቋቋም በምርጫ ሂደት የሚያጋፅሙ ችግሮችን በጋራ በመፍታት ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል፡፡
በሀረሪ ክልል ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ምርጫ ኦሬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ ጌታቸው የጋራ ምክር ቤት መቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ሂደት የሚያጋጥሟቻን ችግሮችን እርስ በእርስ በመመካከርና በመነጋገር ለመፍታት ያስችላል ብለዋል፡፡
ምርጫውንም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ሚናው የላቀ ነው ያሉም ሲሆን በምክር ቤቱ የሚቋቋመው ኮሚቴም በድህረ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ የሚከሰቱ ቅሬታዎችን ለመፍታት እንደሚሰራ ነው የተናገሩት፡፡
በሀረሪ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ሃላፊው አቶ ሐሰን አብዲ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ህግና የስነምግባር ደንብን ባከበር መልኩ እንዲቀሳቀሱ ከማድረግ አንፃር ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
የሀረሪ ክልል የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ መሀመድ ሀሰን አደም በበኩላቸው ምክር ቤቱ መቋቋሙ ምርጫውን ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ እና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ከማድረግ አንፃር አስተዋጽኦው የጎላ ነው፡፡
በሀረሪ ክልል የኢዜማ እጩው አቶ አዝማች ጌጡ እንደተናገሩት የጋራ ምክር ቤቱ መመስረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተናጠል ከሚያደርጉት እንቅስሴ ባለፈ ችግሮቻቸውን በጋራ ለመፍታት እድል ይከፍታል ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.