Fana: At a Speed of Life!

ጥላቻ ተሸንፎ አብሮነትና ፍቅር እንዲጎለብት ህዝበ ሙስሊሙ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል-ም/ጠ/ ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥላቻ ተሸንፎ፣ አብሮነትና ፍቅር እንዲጎለብት ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የበኩሉን እንዲወጣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም÷ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

“በተከበረው የረመዳን ወር የተስተዋሉት መልካም ምግባሮች የዒድ አልፈጥር በዓልን በምታከብሩበት ዕለትም ሆነ በቀጣይ ጊዜያት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አምናለሁም “ብለዋል፡፡

ጽንፈኝት እና ራስ ወዳድነት ያበቀለው ጥላቻ ተሸንፎ፣ አብሮነትና ፍቅር እንዲጎለብት፣ልዩነትን በኃይል የመፍታት ባህል ተስተካክሎ ውይይት – መር ሰላም እንዲሰፍን ሙስሊሙ ማህበረሰብ የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.