Fana: At a Speed of Life!

በሀገር ደረጃ ለማልማት ከታቀደው 13 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት ውስጥ 8 ሚሊየን ሄክታር በዘር ተሸፈነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በመኽር እርሻ ለማልማት ከታቀደው 13 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት ውስጥ እስካሁን 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ግብርና ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው ፥ አሁን እየጣለ ያለው ዝናብም ለመኽር እርሻው ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው።

በ2014/15 የመኽር ወቅት 400 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን በሚኒስቴሩ የሰብል ልማት ዳይሬክተሩ አቶ ኢሳያስ ለማ ተናግረዋል።

ወቅቱ ውጤታማ ይሆን ዘንድም የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ የግብዓት አቅርቦቶች ላይም በክትትል እየተሰራ ነው ብለዋል ዳይሬክተሩ።

በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎችም ግብአት በመንግስት እና በረጂ አካላት እየቀረበላቸው ነው ያሉት አቶ ኢሳያስ ፥ ወደ ልማት እንዲመለሱ እየተሰራ መሆኑን አክለዋል።

የመኽር እርሻ ስራ 90 በመቶ ያህሉ ተጠናቋል ያሉት ዳይሬክተሩ ፥ በዘር ያልተሸፈነው ቀሪ መሬትም እስከ ነሐሴ ወር መጀመሪያ ባለው ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ብለዋል።

በዙፋን ካሳሁን

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.