Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ ደላሎች አማካኝነት ተታለው ወደ ሱዳን ገብተው እስር ላይ የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያን ከእስር ተፈቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጥቅምት ወር በደላሎች አማካኝነት ተታለው ወደ ሱዳን ገብተው ታስረው የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያን ክስ ሳይመሰረትባቸው ከእስር መፈታታቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
 
በኮሚዩኒቲ እና በኤምባሲው አስፍላጊውን ድጋፍ በማድርግ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትና ከቤተስባቻቸው ጋር የሚቀላቀሉበትን መንገድ እየተመቻቸ መሆኑ ተጠቁሟል።
 
ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሱዳንን እንደ መሸጋገሪያ በመጠቀም ወደ ተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ዜጎችንን በማይጨበጥ ተስፋ በመደለልና በማታለል በየጊዜው ብዛት ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ወደ ሱዳን በሕገወጥ መንገድ በማስገባት መንገላታት እንደሚደርስባቸው ተጠቁሟል።
 
ኤምባሲውም ከሚመለከታቸው የሱዳን የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ተጠቂዎችን ከደላሎች መጋዝን እና ከእስር ነጻ በማውጣት ለሀገራቸው እንዲበቁ ሲያደርግ መቆየቱ ይታውሳል፡፡
በመሆኑም ዜጎች መንግስት የስራ ስምምነት ከተፈራረመባቸው ሀገራት ብቻ በሀገር ቤት በመመዝግብ፣ አስፈላጊው የስልጠና ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ወደ ውጭ ጉዞ እንዲያደርጉ ኤምባሲው አሳስቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.