Fana: At a Speed of Life!

ብሪታኒያ ለልማታዊ ሴፍቲኔት የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታኒያ በኢትዮጵያ ለኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ ለመሰረታዊ አገልግሎቶች እና ለልማታዊ ሴፍቲኔት የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ከብሪታኒያ ኮመን ዌልዝ የአፍሪካ ዳይሬክተር ሳይመን ሙስታርድ ከተመራው ልዑክ ጋር ተወያተዋል፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ፣ በአህጉራዊ እና በአለም አቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ እና መሰረታዊ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በልማታዊ ሴፍቲኔት ስራዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው ተመላክቷል፡፡

በውይይቱ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታዋ የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው÷ ድጋፉ በሚሻሻልበት ሁኔታ እና ለተጠቃሚዎች በቀጥታ በሚደርሰበት ጉዳይ ላይ መወያየት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኮመን ዌልዝ የአፍሪካ ዳይሬክተር ሳይመን ሙስታርድ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የድጋፍ መጠን ማደጉን ገልፀው፤ ለወደፊትም የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲሆን ኮመን ዌልዝ የሰውና የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል መግባታቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.