Fana: At a Speed of Life!

በሐረማያ ከተማ በ48 ሚሊየን ብር የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረማያ ከተማ በ48 ሚሊየን ብር የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።
ከፕሮጀክቶቹ ውስጥ የኮብልስቶን ንጣፍ ጨምሮ የገበያ ማዕከልና ጤና ጣቢያ እንደሚገኙበት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሙለታ ቡሽራ ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹም የነዋሪውን ችግሮች እንደሚፈቱ ገልፀዋል።
በተለይም ከተማዋ ካላት ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ የተነሳ በክረምት ወራት ለጎርፍ ተጋለጭነቷ የሰፋ እንደነበር ገልፀው፤ ክረምቱ ሳይገባ ፕሮጀክቶምቹ መጠናቀቃቸው የህብረተሰቡ ጥያቄ ከወዲሁ ምላሽ እንዲያገኝ ያስቻለ ነው ብለዋል፡፡
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አያሌው ታከለ ፕሮጀክቶቹ በዞኑ በመመረቅ ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብለዋል።
የገበያ ማዕከሉም ለአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ እንዲሆን በስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.