በሐረሪ ክልል በአንድ ቀን 100 ሺህ የችግኝ ጉድጓድ ተቆፈረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በሐረሪ ክልል በአንድ ቀን 100 ሺህ የችግኝ ጉድጓድ መቆፈሩ ተገለፀ፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ÷በሐረሪ ክልል በ2014 አረንጓዴ አሻራ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል እቅድ መያዙን ተናግረዋል።
ከሚተከሉት 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ችግኞች ውስጥም 2 ነጥብ 2 ሚሊየኑ ለምግብነት የሚዉሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ይህም የክልሉን የአትክልት ምርትና ምርታማነት እንደሚያሳድገው ተናግረው መላው የክልሉ ነዋሪ የችግኝ ጉድጓድ ዝግጅቱን ከወዲሁ እንዲጀምር ጠይቀዋል።
በክልሉ በዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ ለመትከል በዕቅድ ከተያዘው 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ችግኝ ውስጥ ከ2 ሚሊየን በላይ ችግኞች ዝግጅት በአራት ችግኝ ጣቢያዎቸ ተጠናቋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም