Fana: At a Speed of Life!

በመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ የሚመራ ልዑክ በፈረንሳይ ጉብኝት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የሚመራ ከፍተኛ መኮንኖችን የያዘው የኢትዮጵያ ልዑክ በፈረንሳይ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
 
በጉብኝቱም ከፈረንሳይ የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ሃላፊዎች፣ የመከላከያ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እና የኤታ ማዦር ሹም ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ነው በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያስታወቀው።
 
የልዑካን ቡድኑ የጉብኝት ዓላማ በአየርና በባህር ሃይል ዘርፎች በሚሰጥ ስልጠና እንዲሁም የወታደራዊ ቁሳቁስ አቅርቦትን አስመልክቶ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ያተኩራል ተብሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.