Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን የተከሰተው ጎርፍ ለአርኪዮሎጂ ሥፍራዎች ሥጋት መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሱዳን በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ በዋና ከተማ ካርቱም በስተሰሜን የሚገኙ የአርኪዮሎጂ ሥፍራዎችን በጎርፍ ሊዋጡ እንደሚችሉ ስጋት መፍጠሩ ተገልጿል።
 
ሆኖም ባለስልጣናት የጎርፉን ውሃ ከአካባቢው ለማስወጣትና ቦታውን በአሸዋ በተሞሉ ግድግዳዎች ለመጠበቅ እየሰሩ መሆናቸው ተመላክቷል።
 
በሱዳን የሚገኙ የአርኪዮሎጂ ተመራማሪዎች÷ በጥንታዊቷ ሜሮኤ ስልጣኔ የተገነቡና በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ በአል-ባጅራውያ የሚገኙ የፒራሚዶች ፍርስራሽ ከዚህ ቀደም በጎርፍ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው እንደማያውቅ ገልጸዋል።
 
ትናንት በሰሜን ካርቱም የወንዝ ዳርቻ በሚገኘው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ መኖሪያ አንድ ክፍል ጎርፍ መግባቱም ተገልጿል ።
 
ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትሩና ቤተሰቦቻቸው ከቤት መውጣት እንዳላስፈለጋቸውም ነው የተነገረው።
 
በሱዳን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በዘነበው ከባድ ዝናብ ወደ መቶ የሚጠጉ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል፤ ይህንን ተከትሎም መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል።
 
ምንጭ፡-ቢቢሲ
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.