Fana: At a Speed of Life!

በቀን ከ16 እስከ 18 ሰዓት መጾም ረጅም ዕድሜ ለመኖር እንደሚያስችል አንድ ጥናት አመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀን ከ16 እስከ 18 ሰዓት ከምግብ መቆጠብ ረጅም እድሜ መኖር እንደሚያስችል አንድ ጥናት አመላክቷል።

በኒው ሜዲካል ጆርናል መጽሄት ላይ የወጣው አዲስ የጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በቀን ከ16 እስከ 18 ሰዓት ምግብ ሳይመገቡ ማሳለፍ የተለያዩ የጤና በረከቶችን ያስገኛል።

በዚህ መሰረት በቀን ከላይ ለተጠቀሰው ሰዓት ያህል መጾም ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመቀነስ፣ ከመጠን ያለፈ ክብደትን ለማስወገድ እና ረጅም እድሜ ለመኖር ያስችላል ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈም የካንሰር፣ የስኳር እና የልብ በሽታን እንዲሁም ከመጠን በላይ ውፍረትን ለማስወገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በጥናቱ ተመላክቷል።

ለተጠቀሰው ሰዓት ያክል መጾም በተለይም ከልክ በላይ ለሆነ ውፍረት ለተጋለጡ ሰዎች ሁነኛ መፍትሄ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ሰዎች በቀን ይሄን ያክል ጊዜ ከምግብ ለመቆጠብም ራሳቸውን ማሳመን እና መለማመድ አለባቸው ብለዋል ተመራማሪዎቹ።

ምንጭ ፦ ሲ ኤን ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.