Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ከፍተኛ የፌደራል እና የክልሉ ልዑክ ዛሬ ጅግጅጋ ገብቷል።

በዚህም የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የልዑክ ቡድን በ67 ሚሊየን ብር የተገነባውን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅህፈት ቤት ህንፃ መርቆ ስራ አስጀምሯል።

ርዕሰ መስተዳደርሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት÷ የህንፃው ተጠናቆ ስራ መጀመር አዲሱ መንግስት የህብረተሰቡን ጥያቄ የሚመልስ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

ህንፃው የህፃናት ማቆያን ጨምሮ የዳታ ሴንተር፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽና የአይ ሲ ቲ ላብራቶሪ አካቶ መገንባቱ በክልሉ በዞኑ ደረጃ ካሉ ፅህፈት ቤቶች ለየት እንዲል እደረገው የተናገሩት ደግሞ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ናቸው።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ግርማ አለሙ በበኩላቸው÷ አሁን ግን በ700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ህንፃ መገንባቱ አሰራራችንን እንድናሳልጥ ይረዳናል ብለዋል።

በተመሳሳይ በምስራቅ ሐረርጌ ባቢሌ ወረዳ ከ36 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባው የኢፋ ቦሩ ዋዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ፣ ሱማሌና የሐረሪ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ተገኝተዋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.