Fana: At a Speed of Life!

በቻይና ሻንሺ ክልል በጎርፍ አደጋ 2 ሚሊየን የሚጠጉ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ሰሜናዊ ግዛት በምትገኘው ሻንሺ ክልል የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከ 1 ነጥብ 76 ሚሊየን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
3 ሚሊየን ሄክታር የሚጠጋ የሰብል ማሳ መውደሙም ተመላክቷል።
በመንግስት በተደረገዉ የተደራጀ አሰራርና ብርቱ ጥረት የጎርፍ አደጋው ሊያስከትል የሚችለውን የከፋ ጥፋትለመቀነስ እንደተቻለ ዘገባዉ ያስረዳል፡፡
የአገሪቱ ዜና አገልግሎት ሺንዋ እንደዘገበው÷ በክልሉ በጣለው ኃይለኛ ዝናብ 17 ሺህ ቤቶች ወድመዋል፥ ከ120 ሺህ በላይ ሰዎችም የተፈናቀሉ ሲሆን÷ አደጋው ወደሌለበት አካባቢ እንዲሰፍሩ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል።
የጎርፍ አደጋው ከ70 በላይ በሆኑ ወረዳዎች እና ከተሞች የመሬት መንሸራተትም አስከትሏል።
አውሎ ነፋስ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ ህይወት የማዳን ስራዉን እያደናቀፈው እንደሆነም የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የአሁኑ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የተከሰተዉ በሁናን ግዛት ከባድ ዝናብ ከ300 በላይ ሰዎችን ለሞት ከዳረገ ከሶስት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ መሆኑም ተጠቁሟል።
የቻይናው ሜትሮሎጂ አስተዳደር ለሃገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጸው ÷ የዝናቡ ክብደት እና የአውሎ ነፋሱ ማየል ህይወት የማዳን ስራውን እያደናቀፈ ነው።
የጎርፍ አደጋዉ በርካታ የጥንት ሐውልቶች መገኛ በሆነችዉ ሻንዚም በከፍተኛ ሁኔታ ተከስቷልነው የተባለው፡፡
በመሬት መንሸራተት አደጋው አራት ፖሊሶች መሞታቸዉንም ግሎባል ታይምስ ዘግቧል፡፡
በአመለወርቅ ደምሰው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.