Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪዉ ህዋሃት ለተፈናቀሉ ዜጎች አለማቀፉ ማህበረሰብ እርዳታ እንዲያደርግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ህዳር 18፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲያደርግ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጠየቀ።
በክልሉ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ወረራ ምክንያት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ እያሱ መስፍን እንደገለጹት፥ ከተፈናቃዮቹ ውስጥ 2 በመቶው ብቻ በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን÷ ከተፈናቃዮቹ መካከል 54 ሺህ 354 ህጻናት፣ ከ14 ሺህ በላይ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ይገኙበታል፡፡
ለተፈናቃዮች ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰራ ቢሆንም÷ በቂ ባለመሆኑ ተፈናቃዮቹ በአስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ እንደሚገኙ እና አስቸኳይ ሰብዓ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸዉ ኃላፊው ገልፀዋል።
ህብረተሰቡ ለተቸገሩ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ያጠየቂት ኃላፊው፥ አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች በክልሉ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አስቸኳይ እርዳታ በማድረግ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.