Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚመራ የማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን የሴሮፍታ የእርሻ ልማትን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚመራ የማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ የሴሮፍታ የእርሻ ልማትን ጎበኘ፡፡
በኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ስር የሚገኘው ይህ የእርሻ ልማት ቦታ ባለፉት አምስት ዓመታት ሳይለማ የቀረና በአሁኑ ሰዓት በ 2 ሺህ 800 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ተዘርቶ እንክብካቤ እየተደረገለት ይገኛል፡፡
ከዚህ ውስጥ ከ25 ሄክታር በላይ በኩታ ገጠም እየለማ እንደሚገኝ የክልሉ ግብር እና የተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ተናግረዋል፡፡
ላለፉት ዓመስት አመታት ሳይለሙ የቆዩትን የጎፈር፣ሻሎ እና ሴሮፍታ የእርሻ ልማት ላይ ስንዴ እና ገብስ ጨምሮ 9 እህል ዝርያዎችን እየተመረቱ እንደሆነ አቶ ጌቱ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.