Fana: At a Speed of Life!

በአዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከአምራቾች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በአዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከአምራቾች ጋር ተወያየ።

አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወሳል።

ይህን በተመለከተም ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው የተለያዩ አምራቾች ጋር ተወያይቷል።

የኤክሳይስ ታክስ ምንነትና ታሪካዊ ዳራ፣ ኤክሳይስ ታክስ የሚጣልባቸው እቃዎችና አገልግሎት ባህርያት፣ ኤክሳይስ ታክስ የሚጣልበትና የማሻሻያው ምክንያት እንዲሁም የረቂቅ አዋጁ ዋና ዋና ገጽታዎችን በተመለከተ የመወያያ ሰነድ ቀርቧል።

በውይይቱ ኤክሳይስ ታክስ በአግባቡ መከፈልና አለመከፈሉን መቆጣጠር የሚያስችል የኤክሳይስ ቴምብር የሚለጠፍባቸውና አምራቾች በሚያመርቱበት ወቅት ለሚያጋጥማቸው የምርት ብልሽት፥ በተበላሸው ምርት ያልተገባ የኤክሳይስ ታክስ እንዳይከፍሉና ለአላስፈላጊ ወጪ እንዳይዳረጉ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

እንዲሁም የኤክሳይስ ታክስ የሚከፈልበትና የማይከፈልበት ስለመሆኑ ለመለየት የሚያስችል ቴምብር በምርታቸው ላይ የሚለጥፉበትን ስርዓት ለማምጣት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.