Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል ላስመዘገበው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የማበረታቻና የእውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የማበረታቻና የእውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ማምሻውን ባዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

መንግሥት በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች ከ50 ሺህ ብር እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚደርስ ሸልማት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ በተገኙበት ማበርከቱ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡት አትሌቶች የ10 ሚሊየን ብርና የመሬት ስጦታ ማበርከቱ ይታወቃል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.