Fana: At a Speed of Life!

በጃፓን ሌላ አይነት የኮሮና ቫይረስ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጃፖን ሌላ አይነት የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በብሪታኒያ እና ደቡብ አፍሪካ ከተገኘው የኮሮና ቫይረስ ጋር በከፊል ተመሳሳይነት ያለው ቫይረስ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የጃፓን የጤና ሚኒስቴር ቫይረሱ ከብራዚል ከመጡ አራት ሰዎች ላይ እንደተገኘ ነው ያስታወቀው።

ብሄራዊ የተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲትዩት እስከ አሁን ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ እንደሌለ ገልጿል።

እንዲሁም ቫይረሱ ከባድ ምልክቶች እንዳሉት እና የኮሮና ቫይረስ ክትባትን መቋቋም አለመቋቋሙ ለማወቅ የሚያስችል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ማስታወቁን የጃፓን ታይምስ ዘገባ ያሳያል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል የ40 ዓመቱ ግለሰብ ከብራዚል ጃፓን በደረሰበት ወቅት ምንም አይነት ምልክት ያልነበረው ቢሆንም ከቆይታ በኋላ የመተንፈስ ችግር አጋጥሞት ሆስፒታል እንደገባ በዘገባው ተጠቅሷል።

ሌላኛው የ30 ዓመት እድሜ ያላት ሴት ደግሞ የእራስ ምታት ምልክት ፤ ከ10 እስከ 19 እድሜ ውስጥ የሚገኘው ታዳጊ ትኩሳት እንዲሁም በተመሳሳይ የእድሜ ክልል ውስጥ የምትገኘው ታዳጊ ምንም አይነት ምልክት አለማሳየቷ ተነግሯል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.