Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ ለአገር መከላከያ ሰራዊት 12 ሚሊየን ብር ተሰበሰበ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ ለአገር መከላከያ ሰራዊት 12 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ።

የከተማው ከንቲባ አቶ ነጂብ አባ ራያ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደ ተናገሩት፥ የከተማው ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት በአይነትና በገንዘብ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚህም ከከተማው ነዋሪዎች 12 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የገለፁት ከንቲባው 10 ሚሊየን ብር ለሰራዊቱ ድጋፍ በተዘጋጀ አካውንት መግባቱንና የቀረውም በቅርቡ ከሌሎች የአይነት ድጋፍ ጋር ለሰራዊቱ እንደሚላክ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም ለሰራዊቱ ድጋፍ የሚውል በ900 ሺህ ብር የተገዙ በሬዎችና በከተማው ሴቶች 120 ኩንታል ስንቅ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

የከተማው ነዋሪዎች ደጀንነታቸውን ለማረጋገጥ ለሰራዊቱ የሚያደርጉት ድጋፍ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባው ተናግረዋል።

በሙክታር ጠሃ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.