Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ሳቢያ የሚፈጠረውን የኢኮኖሚ ጫና በዘላቂነት ለመፍታት በአፍሪካ ያለውን ሰፊ የገበያ እድል መጠቀም ይገባል- አቶ ክቡር ገና

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በጦርነቱ ሳቢያ ሊያጋጥማት የሚችለውን የኢኮኖሚ ጫና በዘላቂነት ለመፍታት በአፍሪካ ያለውን ሰፊ የገበያ አማራጭ በመጠቀም መስራት እንዳለባት የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ክቡር ገና ገለጹ፡፡

በውጭ አገራት ያሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በህልውና ዘመቻው የፈጠሩትን አንድነት የኢኮኖሚ ጫናውን ለማካካስ መጠቀም እንደሚገባም ነው የጠቆሙት፡፡

አሸባሪው የሕወሃት ቡድን ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማ አንግቦ በሰሜን እዝ የሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት በማድረስ አገሪቷን ወደ አልተፈለገ ጦርነት ካስገባት በኋላ[፥ አንዳንድ የምእራባውያን አገራትና ለጋሽ ድርጅቶች ብድር ከመከልከል ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ የኢኮኖሚ ጫና የሚፈጥሩ አካሄዶችን በመከተል ዓላማቸውን ለማስፈጸም ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡

የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤቶች ዋና አስተዳዳሪና የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ክቡር ገና ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በጦርነቱ ሳቢያ ሊከሰቱ የሚችሉ የኢኮኖሚ ጫናዎችን ለመቀነስ የተለያዩ ዘዴዎችን ቀይሶ መንቀሳቀስ ይገባል፡፡

የኢኮኖሚ ማካካሻ ስራዎች ተገቢውን ጥናት መሰረት ያደረጉ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰው፤ በተለይ ለአገር ውስጥ አቅም ትኩረት መሰጠት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የተደቀነው አደጋ ለመመከት በውጭ እና አገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን በአንድነት መቆማቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይህንን ትብብር በኢትዮጵያ ላይ የሚደረሰውን የኢኮኖሚ ጫና ለመከላከል መጠቀም እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ኢኮኖሚውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሻሻል ከሚተገበሩ ስራዎች ጎን ለጎን በአፍሪካ ያለውን ሰፊ የገበያ እድል መጠቀም ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

አፍረካ ካላት የወጣት የሰው ሃይል ቁጥር አንጻር በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁ የገበያ መዳረሻ የመሆን አቅም እንዳላትም አብራርተዋል፡፡

ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ አገራት ትልቅ እድል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.