Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ሁለት ወራት ከ600 በላይ የአቅመ ደካማ ቤቶች መጠገናቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ሁለት ወራት ከ600 በላይ የአቅመ ደካማ ቤቶች ከበጎ ፈቃደኛ ወገኖች ጋር በመሆን መጠገናቸውን ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታወቁ፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ እንዳስታወቁት ከበጎ ፈቃደኛ ወገኖች ጋር በመሆን ባለፉት ሁለት ወራት ከ600 በላይ የሚሆኑ የአቅመ ደካማ ቤቶች የተጠገኑ ሲሆን÷ ዛሬም ብዙዎች የኛንና የናንተን ድጋፍ ይፈልጋሉ ብለዋል።

ለዚህም ለሁላችሁም የከተማችን ነዋሪዎች ከራሳችን በላይ አሻግረን እንድናይ፣ ጎረቤቶቻችንን እንድንደግፍ፣ ጎጆአቸው ያዘመሙ ወገኖቻችንንም ቤታቸውን በጋራ እንጠግንላቸው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለኛ ትንሽ ነው ብለን የምናስበው ለነሱ ግን ትርጉሙ ብዙ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.