Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 604 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ 7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 8 ሺህ 348 የላብራቶሪ ምርመራ 604 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 71 ሺህ 687 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው ዕለታዊ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ባለፈ ባለፉት 24 ሰዓታት የ 7ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 148 ደርሷል።

እስካሁን ድረስ 1 ሚሊየን 234 ሺህ 645 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 41 ሺህ 76 ሲሆኑ፥ ከእነዚህም ውስጥ 267 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በዛሬው እለትም 208 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን ÷በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 29 ሺህ 461 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.