Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ተዘዋውሮ ተመለከተ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ መብት አያያዝ ተመልክቷል፡፡
ቦርዱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ እና በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ሰብኣዊ መብት አያያዝ ምን እንደሚመስል ነው ተዘዋውሮ የተመለከተው፡፡
በምልከታው ወቅት ተጠርጣሪዎቹ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳልደረሰባቸው የገለጹ ሲሆን፥ የተጠረጠሩበት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲጣራላቸው ጥፋተኛው ተለይቶ እንዲጠየቅ እና ንፁሃን ሰዎች ደግሞ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ በበኩላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት አለመኖሩ ጥሩ ሆኖ የተነሱትን ቅሬታዎች ግን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚነጋገሩባቸው ገልፀዋል።
ተጠርጣሪዎች በሚገኙባቸው ማቆያ ቦታዎች አልፎ አልፎ የውሃ መቆራረጥ ቢኖርም ችግሩን ለማስተካከል ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር እንደሚሰራም ገልጿል።
ቦርዱ በቀጣይም የተጠርጣሪዎቹ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ሕጋዊ ያልሆኑ አሰራሮች ካጋጠሙ ከስር ከስር እየተከታተለ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው በተዋረድ ካለው መዋቅር ጋር በትብብር እንደሚሰራ መግለጹን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.