Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች እስከ መጋቢት 3 እንዲያሟሉ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲያሟሉ አሳሰበ።

በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ምርጫ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት በቦርዱ ሀገር አቀፍ እና የክልል ፓርቲዎች ማሟሟላት ያለባቸውን ግዴታ ለማስፈጸም የወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2012 መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ማሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያስረዱ ሰነዶች ማዘጋጀቱ እና ለፓርቲዎች እንዲደርሳቸው ማድረጉን አስታውሷል፡፡

ለእያንዳንዱ ፓርቲም በደብዳቤ ሟሟላት የሚገባቸውን ሁኔታዎች ሁሉ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ አሟልተው እንዲያቀርቡ እንዳስታወቀ ተጠቁሟል።

ሆኖም እስካሁን ሰነዶቻቸውን ያስገቡ ፓርቲዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን ቦርዱ በዛሬው ዕለት ገልጿል።

በመሆኑም ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ዝርዝር ሁኔታዎች የሚያስረዱ ሰነዶች የደረሳቸው የፓለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ከመድረሱ በፊት ማሟላት የሚገባቸውን በሙሉ አሟልተው የምዝገባ ስርአቱን እንዲጀምሩ አሳስቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.