Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 566 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 944 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ5 ሺህ 278 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 566 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
 
ሚኒስትሯ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 282 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም 944 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ 960 ደርሷል፡፡
 
ባለፉት 24 ሰአታት የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 238 መድረሱን ገልጸዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም 944 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ 960 ደርሷል፡፡
 
ባለፉት 24 ሰአታት የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 238 መድረሱን ገልጸዋል፡፡
 
እስካሁን በኢትዮጵያ ለ1 ሚሊየን 312 ሺህ 910 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 80 ሺህ 3 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
 
ከዚህ ውስጥ ቁጥር 34 ሺህ 960 ከቫይረሱ ሲያገግሙ 44 ሺህ 803 ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ አለባቸው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.