Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 703 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 550 ሰዎች አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ7 ሺህ 151 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 703 ሰዎ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ 89 ሺህ 137 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት 550 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ 42 ሺህ 649 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በተጨማሪም የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 352 መድረሱንም ገልጿል።

በቫይረሱ ሳቢያ 281 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

እስካሁን በኢትዮጵያ ለ1 ሚሊየን 397 ሺህ 348 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 89 ሺህ 137 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ ውስጥ 45 ሺህ 134 ሰዎች ቫይረሱ ሲኖርባቸው 42 ሺህ 649 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.