Fana: At a Speed of Life!

ቻይና  ሰዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ መሆን አለመሆናቸውን  የሚለይ መተግበሪያ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣የካቲት 3፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና ሰዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ መሆን አለመሆናቸውን የሚለይ መተግበሪያ ይፋ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡

መሳሪያው ሰዎች በአቅራቢያቸው  በቫይረሱ የጠጠቃ ሰው ወይም ተጠርጣሪ መኖሩ አለመኖሩን ማወቅ እንዲችሉ ያስችላል ተብሏሎ።

አዲስ የተተገበረው ይህ ቴክኖሎጂው የቻይና መንግስት ሕዝቡን  በቅርብ  ለመከታተል እንደሚያግዘውም ተገልጿል፡፡

ደንበኞች ጥያቄ ለመጠየቅ መተግበሪያዎችን በመጠቀም በስማርት ስልኮቻቸው ላይ  እንደ የክፍያ አገልግሎት ወይም  በዊቻት ፈጣን ምላሽ ኮድን መቃኘት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡

ይህ  መተግበሪያ በስልክ ቁጥር አንዴ ከተመዘገበ በኋላ ተጠቃሚዎች ስማቸውን እና መታወቂያ ቁጥራቸውን የሚያስገቡ ሲሆን÷እያንዳንዱ የተመዘገበ የስልክ ቁጥር እስከ ሦስት  በሚደርሱ የመታወቂያ ቁጥሮች ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት  እንደሚያገለግልም ነው የተነገረው፡፡

የቻይና መንግስት በዜጎቹ ላይ ከፍተኛ  ክትትል እንደሚያደርግ በሰፊው የሚታወቅ ቢሆንም በመስኩ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይህ  መተግበሪያ በሀገሪቱ ውስጥ አወዛጋቢ ሆኖ አልታገኘም ተብሏል፡፡

መቀመጫውን ሆንግ ኮንግ ያደረገው ቴክኖሎጂ ድርጅት ጠበቃ የሆኑትፓይፐር ካሮሊን ቢግ  በቻይናና በኢስያ መረጃ ታፍኖ የሚቀመጥ ሳይሆን ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ነገር ነው ብለዋል፡፡

በተፈለገበት ቦታ ሁሉ ግልጽ በሆነ መንገድ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡

ባለሞያዋ አክለውም  ከቻይናዊያን  አንጻር ይህ መተግበሪያ   ጠቃሚ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን÷  መረጃዎች ለመልካም ነገር ጥቅም ላይ ሲውሉ ያላቸውን ሀይል ትረዳለህ ብለዋል፡፡

መተግበሪያው በመንግስት  እና በቻይና ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ቡድን ኮርፖሬሽን በጋራ የተሰራ ሲሆን ከጤና እና ትራንስፖርት ባለስልጣናት በተገኘው መረጃ የተደገፈ መሆኑንም ነው የተገለጸው፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.