Fana: At a Speed of Life!

የስራ ፈጠራን የሚደግፈው ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የስራ ፈጠራና ስታርትአፕን የሚደግፈው ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡

ኢኒሼቲቩ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም አነሳሽነት በአፍሪካ በተለይ ኢንቨስትመንትን፣ ስራ ፈጠራንና ስታርትአፕን ለመደገፍ የሚሰራ ነው።

ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በአህጉሪቱ ግዙፍ የፓንአፍሪካ ስታርትአፕ ምህዳር መፍጠርን ያለመ ነውም መባሉን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

በኢንሼቲቩ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ባሳለፍነው ጥር ወር በስዊዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በመሆን ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭን ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ነው።

ኢኒሼቲቩ 1 ቢሊየን ዶላር ሀብት በማሰባሰብ የ100 ሚሊየን አፍሪካውያንን ህይወት ለማሻሻልና ለ10 ሚሊየን ሰዎች የስራ ዕድል የመፍጠር ግብ አስቀምጧል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.