Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ጦርነት አትፈራም – ዢ ጂንፒንግ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሀገራቸው ጦርነት እንደማትፈራ እና የሉዓላዊነት፣ የደህንነት እና የልማት ፍላጎቷ ዝቅ ተደርጎ እንዲገመት እንደማትፈቅድ ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ የቻይና ጦር ወደ ኮሪያ ጦርነት የገባበትን 70ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ቤጅንግ በሚገኘው ታላቁ የቻይና ህዝብ አዳራሽ ንግግር አድርገዋል።

ለብቻ የሚወሰን ውሳኔ፣የአንድ ወገን የኢኮኖሚ የበላይነት እና ጠብ አጫሪ ድርጊት ምንም ሊሰራ አይችልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ወደ ሞት ብቻ ሊመራ የሚችል ጉዳይ ነው ብለዋል።

ዓለም ሊያውቀው የሚገባው ነበር በአሁኑ ወቅት የቻይና ህዝብ ተደራጅቷል ፣ ላይከበር የሚችልበት ሁኔታ የለም ሲሉ የቻይና መስራች አባት ማኦ ዜዶንግን በመጥቀስ ንግግር አድርገዋል።

ምንም እንኳን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በዘመናቸው የመጨረሻ ላይ የደረሰ ቢሆንም በዚህ ንግግራቸው የአሜሪካን ስም አልጠቀሱም።

ሁለቱ ሃያላን ሀገራት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከቴክኖሎጂ፣ ንግድ እና ደኅንነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከባድ ግጭት ውስጥ መግባታቸው የሚታወስ ነው።

ከ70 ዓመት በፊት አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ ጋር በመሆን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን ይህንን ተከትሎ ቻይና 2 ሚሊየን የሚሆኑ ወታደሮቿን ወደ ሰሜን ኮሪያ አስገብታ ነበር።

ምንጭ÷ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.