Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካ ከተደረመሰ ሕንፃ ውስጥ 11 ሰራተኞች በህይወት ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ከተደረመሰ ሕንፃ ውስጥ 11 ሰራተኞች በህይወት መገኘታቸው ተሰምቷል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ጆርጅ ከተማ በግንባታ ቦታ ላይ የነበረ ግዙፍ ፎቅ ሕንጻ የተደረመሰ ሲሆን ፥ 75 ሰዎች እዚያ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

በዚህ ፍለጋም አነፍናፊ ውሾችን ጨምሮ የነፍስ አድን ሃይሎች ተሰማርተዋል ተብሏል፡፡

እስካሁንም 11 ሰዎች በህይዎት እንደተገኙ የተነገረ ሲሆን፥ በአንጻሩ በአደጋው የሠባት ሰዎች ህይዎት ማለፉ መረጋገጡን የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በፍርስራሹ ውስጥ የሚገኙትን ከ30 በላይ ሰዎች ለማዳን ሙከራ እየተደረገ እንደሆነም ነው የተነሳው፡፡

ሆኖም አደጋው ካደረሰው ከባድ ጉዳት አንጻር የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.