Fana: At a Speed of Life!

ከሀዋሳ አዲስ አበባ በሚበር አውሮፕላን ጭስ ቢታይም መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ወርደዋል – አየር መንገዱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሀዋሳ አዲስ አበባ በሚበር አውሮፕላን ጭስ ቢታይም መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

የበረራ ቁጥር ኢቲ 154 ዛሬ ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ አውሮፕላኑ ውስጥ ጭስ ታይቷል።

ይሁን እንጂ አውሮፕላኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በመቆም መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ደንበኞቹን ይቅርታ መጠየቁን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣው መረጃ ጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.