Fana: At a Speed of Life!

በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ኬንያውያን አስቸኳይ ድጋፍ ሊቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ በናይሮቢ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው እያንዳንዱ ቤተሰብ የአስቸይ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያቀርቡ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ የጎርፍ አደጋ የደረሰባቸውን አካባቢዎች የጎበኙ ሲሆን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ለእያንዳንዱ ጉዳት ለደረሰበት ቤተሰብ የ10 ሺህ ሽልንግ (75 ዶላር) ድጋፍ እንደሚደረግ እና በጎርፉ የወደሙ ትምህርት ቤቶችም እንደሚገነቡ ቃል ገብተዋል፡፡

ትምህርትቤቶች ዳግም ከመከፈታቸው በፊትም በጎርፍ የተጎዱ ሁሉንም ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት 1 ቢሊየን ሽልንግ (7 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር) መመደቡን አስታውቀዋል፡፡

በሀገሪቱ የዘነበው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እስከ አሁን ከ200 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና አሁንም ዝናቡና ጎርፉ በመቀጠሉ በዚህ ሣምንት ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የተያዘው ዕቅድ መራዘሙን ገልጸዋል፡፡

በናይሮቢ አሁን ጉዳት እንደደረሰበት ዓይነት መደበኛ ባልሆነ መንገድ በተመሰረቱ መንደሮች የሚኖሩ ዜጎችን ለመደገፍም የ20 ሺህ ቤቶችን ግንባታ ይፋ ማድረጋቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.