Fana: At a Speed of Life!

አለም አቀፉ የፅዳት ቀን በአዲስ አበባ በፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አለም አቀፉ የፅዳት ቀን በአዲስ አበባ በፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተከበረ።

ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ በመንግስት ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች እና በሀይማኖት ተቋማት የፅዳት መርሃግብር ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በርካታ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች በየአካባቢያቸው በንቅናቄው ተሳትፈዋል።

ወይዘሮ አዳነች በዛሬው እለት ከ1 ሚልዮን በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የአለም ማህበረሰብን በመቀላቀል አካባቢያቸውንና ከተማቸውን እያፀዱ መሆኑን ተናግረዋል።

በዛሬው እለት ትምህርት ቤቶችን የማጽዳት እና የጸረ ተሕዋሲያን ኬሚካል ርጭት ስራ መካሄዱንም ነው ያመለከቱት።

“ባሳለፍነው ዓመት ታትረው የጽዳት ስራ ሲሰሩ የነበሩ ነዋሪዎቻችንን እያመሰገንኩ ከዛሬ ጀምሮ ሁላችንም በመተባበር እና በአንድነት መንፈስ አዲስ አበባ ስሟን እና ክብሯን የሚመጥን ጽዳት እንዲኖራት በእንዲህ ቀን ዘመቻ ሳይሆን ሁሌም በማጽዳት ለነዋሪዎቿ ምቹ ለቱሪዝም ሳቢ ከተማ እድናደርጋት ጥሪዬን አቀርባለው” ብለዋል በመልዕክታቸው።

በዛሬው ፅዳትን በመጠበቅ የተሻለ አፈፃፅም ያላቸው አካባቢዎች እውቅና እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.