Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት አልማዝ ኃይሌ ከዚህ አለም በሞት ተለየች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በበርካታ የትያትርና ፊልም ስራዎች የምትታወቀው አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።
ባለፉት ሁለት ሳምንታት የህክምና ክትትል ሲደረግላት የቆየችው አርቲስት አልማዝ በዛሬው ዕለት ህይወቷ አልፏል።
አርቲስት አልማዝ ለ42 ዓመታት በብሄራዊ ትያትር ቤት በተዋናይነት፣ ተወዛዋዥነት እና ሜካፕ አርቲስትነት ማገልገሏ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው።
እንዲሁም ከብሄራዊ ትያትር ቤት ተሳትፎዋ ባሻገር በበርካታ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራሞች፣ ፊልሞች እና ማስታወቂያዎች ላይ ተሳትፎ አድርጋለች።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.