Fana: At a Speed of Life!

አንድነታችንን ሊበትን የመጣውን ወራሪ የህወሓት ሃይል ለመጨረሻ ጊዜ ማባረር አለብን – አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር መስራች ጉባኤ ላይ አዲስ የተመረጡት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
በወቅቱ ከልዩነት ይልቅ አንድነታችንን የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ልናተኩር ይገባል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡
አንድነታችንን ሊበትን የመጣውን ወራሪ የህወሓት ሃይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማባረር ቀሪ ስራችንን ማጠናቀቅ አለብን ብለዋል።
በመሆኑም የምክር ቤቱ አባላት መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይል እና ሚሊሻዎችን በማጠናከር ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.