Fana: At a Speed of Life!

አዲስ ቻምበር 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡
ንግድ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ የንግድ ምክር ቤቶች ታሪክ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፍ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አዲስ ቻምበር የተመሰረተበት 75ኛ ዓመት በዓል ከሰኔ 21 እስከ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የሚከበር ሲሆን ለሦስት ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
በኢትየጵያ የግሉ ዘርፍ ልማትና ከባቢ የፖሊሲ ሁኔታዎች፣ ህገወጥ ንግድና የተወዳዳሪነት ፈተናዎች፣ የህጎችና ደንቦች አወጣጥ በግሉ ዘርፍ ልማት፣ የቢዝነስ መጻኢ እድሎች እንዲሁም የንግድ ማህበራትና ተቋማት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸው ሚና የሚሉት ፓናሎቹና ሲምፖዚየሞች የምስረታ በአሉን አስመልክቶ ይከወናሉ ተብሏል፡፡
በማህሌት ተክለብርሃን
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.