Fana: At a Speed of Life!

ኢሚሬትስ አየር መንገድ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሁሉንም የመንገደኞች በረራ አቋረጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢሚሬትስ አየር መንገድ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ሁሉንም የመንገደኞች በረራ ላልተወሰነ ጊዜ አቋረጠ።

የኢሚሬትስ አየር መንገድ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ፥ በሁሉም የዓለም አቀፍ መዳረሻዎች የሚያደርጋቸው የመንገደኞች በረራዎች ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ይቆማሉ ብሏል።

የመንገደኞች በረራዎች ቢቋረጡም ሁሉም የጭነት (ካርጎ) በረራዎች ግን እንደሚቀጥሉ ነው አየር መንገዱ በመግለጫው ያስታወቀው።

በበረራዎች መቋረጥ ለሚፈጠረው መስተጓጎል ደንበኞቹን ይቅርታ የጠየቀው አየር መንገዱ፤ በመንገደኞች ላይ የሚፈጠሩ ጫናዎችን ለመቀነስ እንደሚሰራም ነው የገለፀው።

በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሁሉም የኢሚሬትስ ግሩፕ ሰራተኞች ከስራቸው እንደማይፈናቀሉም ነው ያስታወቀው።

የአየር መንገዶች እና የጉዞ ኢንዱስትሪ በተለያየ ጊዜ ችግሮች ያጋጥሙታል ያለው ኢሚሬትስ አየር መንገድ፤ በመንገዶኞቹ ድጋፍ ሁሉንም ይታለፋል ብሏል።

አሁን ላይ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዘው ያሉ ጉዳዮችን በቅርበት እንደሚከታተል የገለፀው አየር መንገዱ፤ ሁኔታዎች በሚፈቅዱት ፍጥነት ወደ ስራ እንደሚመለስም አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.