Fana: At a Speed of Life!

ኢማኑኤል ማክሮን ምዕራባውያን ካከማቹት የኮሮና ክትባት ከ4 እስከ 5 በመቶውን ለታዳጊ ሃገራት እንዲሰጡ ጠየቁ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሀብታም ሃገራት ካከማቹት የኮሮና ቫይረስ ክትባት 5 ከመቶውን ለታዳጊና ድሃ ሃገራት እንዲሰጡ ጠየቁ፡፡
ማክሮን የቡድን ሰባት አባል ሃገራት በበይነ መረብ ከሚያካሂዱት ስብሰባ ቀደም ብሎ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ እንደገለጹት ክትባቶችን በአግባቡ አለመካፈል የዓለምን እኩልነት ያጠፋል ፡፡
እስካሁንም አብዛኛው ክትባት እየተሰጠ ያለው ከፍተኛ ገቢ ላላቸው ሃገራት መሆኑም ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኮቫክስ የሚባለውን ክትባት ለታዳጊና ድሃ ሃገራት ለማድረስ ለሚሰራው ጥምረት 4 ቢሊየን ዶላር ይለግሳሉ ተብሏል፡፡
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም ክትባቶችን ለኮቫክስ እንደሚለግሱ ይጠበቃል፡፡
እስከዛሬ በዓለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ ከ110 ሚሊየን ሰዎች በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በአፍሪካ ደግሞ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.