Fana: At a Speed of Life!

ፑቲን ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልምምድ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታክቲካል (ስልታዊ) የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልምምድ እንዲደረግ ለሀገሪቱ ጦር ትዕዛዝ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡

ልምምዱ አንዳንድ ምዕራባውያን ባለስልጣናት የሚሰነዘሩትን ጠብ አጫሪ መግለጫ እና ዛቻ ተከትሎ የሚካሄድ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ትዕዛዙን ተከትሎ ሩሲያ ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎቿን የማድረግ አቅም በቅርቡ መፈተሽ ትጀምራለች፡፡

በልምምዱ የደቡብ ወታደራዊ ዲስትሪክት ሚሳኤል ሃይሎች፣ ወታደራዊ አውሮፕላኖች እና የሩሲያ የባህር ኃይል እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡

ልምምዱ ስልታዊ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን አቅም ለመፈተሽ እና በተመረጡ ቦታዎች ለማሰማራት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን÷ ሩሲያ የግዛት አንደነቷንና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የሀገሪቱ ጦር በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጣቸውንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.