Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶች ከአገር እንዲወጡ ወሰነች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶች ከአገር እንዲወጡ መወሰኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት: ዲፕሎማቶቹ በአዲስ አበባ አየርላንድ ኤምባሲ ይሰሩ የነበሩ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን በሣምንት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ተወስኗል።
 
የአሁኑን ብሄራዊ ተልዕኮ የሚመጥን አወካከል መፍጠር በማስፈለጉና የአገራችን ብሄራዊ የህልውና ዘመቻ ይበልጥ እንዲሳካ ለማድረግ እርምጃው መወሰዱን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።
 
አክለውም ሌሎች የኤምባሲው ሰራተኞች መደበኛ ስራቸውን እንደሚሰሩና ኤምባሲውም አገልግሎቱን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
 
አየርላንድ በጸጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በመፃረርና አሸባሪውን ህወሓት በመደገፍ ጠንካራ አቋም በመያዝ ጫና ስትፈጥር መቆየቷ ይታወሳል።
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.