Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል እና የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የመጀመሪያውን የቀረጥ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል እና የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የመጀመሪያውን የቀረጥ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የእስራኤል የገንዘብ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፥ ሃገራቱ የኢንቨስትመንት ጥበቃን ያካተተና የመጀመሪያ የሆነውን የቀረጥ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በሃገራቱ መካከል የሚደረገውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ከማሳደግ ባለፈ ተደጋጋሚ ቀረጥን ለማስቀረት እንደሚረዳ የሚኒስቴሩን መግለጫ ዋቢ ያደረገው የሺንዋ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሃገራቱን የንግድ ልውውጥ ለማሳለጥና የቢዝነስ ትብብራቸውን ለማሳደግ ያግዛልም ነው የተባለው፡፡

ፍትሃዊ የንግድ ልውውጥን ማድረግ፣ የመረጃ ልውውጥን ጨምሮ በንግድ ልውውጥ ወቅት ቀረጥ መቀነስን አላማው ያደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ሁለቱ ሃገራት በፈረንጆቹ መስከረም ወር 2020 ላይ በዋሽንግተን አደራዳሪነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ መስማማታቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.