Fana: At a Speed of Life!

እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚሰፍነው በሀገራት ላይ ጣልቃ ገብነት ሲቆምና ህዝቡ የራሱ ዴሞክራሲ ባለቤት ሲሆን ነው – ዋንግ ዪ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ÷ አንድ የዴሞክራሲ ዓይነት ብቻ የለም ፤ ይልቁንም እውነተኛ የዴሞክራሲ መንፈሥ ለማስፈን እንሥራ ሲሉ በ14ኛው የባሊ የዴሞክራሲ መድረክ ላይ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ዋንግ ዪ በበይነ መረብ በተካሄደው የዴሞክራሲ መድረክ ላይ እንደተናገሩት ፥ ቅድመ አያቶቻችን እኛ የሰው ልጆች ከጦርነት ነጻ የሆነ፣ ረሃብና ድህነት ያላገኘው፣ በፍትህ ላይ የተመሠረተ ደስተኛ ሕይወት እንድንኖር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ላለፉት ሺህ ዓመታት የተሻሉ ስርዓቶች እና የፖለቲካ አወቃቀሮች ላይ ሠርተዋል፡፡

ዛሬ ፈልገን የምናሳድደውን ዴሞክራሲ እነሱ ቀድመው ሰርተውታልም ብለዋል የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡

በበይነ መረብ በተካሄደው ውይይት ላይ አንድ የቻይና ዲፕሎማት በሰጡት አስተያየትም “አንዳንዶች የአንድን አገር የዴሞክራሲ ሞዴል እንደ አይነኬ መሥፈርት በመውሰድ ለመተግበር ሲጥሩ በዓለም የዴሞክራሲ ሥርዓቶች እና ርዕዮተ ዓለሞች መካከል ውጥረት በመቀስቀስ ለመለያየት እና ግጭት መንስኤ ሲሆኑ ይስተዋላል” ብለዋል፡፡

እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚሰፍነው በሀገራት ላይ ጣልቃ ገብነት ሲቆም እና ህዝቡ የራሱ ዴሞክራሲ ባለቤት ሲሆን ነው ማለታቸውንም ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.