Fana: At a Speed of Life!

ከኢትዮጵያ ጎን መቆም ከአፍሪካውያን የወደ ፊት እጣ ፋንታ ጋር አብሮ መቆም ነዉ- ቢልለኔ ስዩም

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በምዕራባውያን ጣልቃ ገብነትና ጫና እየተፈተነች ባለችበት በዚህ ጊዜ ከኢትዮጵያ ጎን መቆም ከአፍሪካዉያን የወደ ፊት እጣ ፋንታ ጋር አብሮ መቆም መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናገሩ።

ሃላፊዋ “ኒዉስ ሩም አፍሪካ” ከተሰኘው የደቡብ አፍሪካው ዲጂታል የሳተላትይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በአሸባሪው ህወሓት የተከፈተውን ጦርነት ለግል የፖለቲካ ፍላጎታቸው ማስፈፀሚያ ለማድረግ የሚፈልጉ የዉጭ ሃይሎች፥ ለወራሪው ቡድን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ የሳተላይት መረጃ እየሰጡ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካዉያን ነፃነት ቀንዲል መሆኗን የተናገሩት ሃላፊዋ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መደፈር የአፍሪካ ሉዓላዉነት መደፈር ነዉ ብለዋል፡፡

በመሆኑም በዚህ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን መቆም ለአፍሪካዉያን የወደፊት እጣ ፋንታም አብሮ መቆም መሆኑን ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ስልጣን ተቆጣጥሮ በነበረባቸዉ ጊዜያት በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀመዉ አሸባሪዉ የህዋሓት ቡድን በህግ ማስከበር ዘመቻዉ እርምጃ የተወሰደበት ቢሆንም በዉጭ ሃይሎች በሚደረግለት እርዳታ ቡድኑ ከእንደገና ራሱን በማደራጅት የአፋርና የአማራ ክልሎች ላይ ወረራ መፈጸሙንም ሃላፊዋ አብራረተዋል፡፡

አዲስ አበባ በሽብር ቡድኑ ተከባለች በሚል ሲኤንኤንን ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባውያን ሚድያዎች ከሳምንት በፊት ያሰራጩት ሃላፊነት የጎደለው የሀሰት ዘገባ መሆኑን ገልጸው ÷ ህዝብን ለማሸበር ሆንብለው የሰሩት የተቀናጀ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ስራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም እውነታው እነዚህ አካላት እንደሚያራግቡት ሳይሆን አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ሰላማዊ እንቅሰቃሴ መኖሩንና ከተማዋ ሰላም መሆኗ ሊታወቅ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.