Fana: At a Speed of Life!

ክፍለ ከተማው ለህልውና ዘመቻው ያሰባሰበውንድጋፍ እያስረከበ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቦሌ ክፍለ ከተማ ለሀገር ክብር ለሚዋደቀው መከላከያ ሠራዊት ያሰባሰበውን ድጋፍ የማስረከብ መርሃ ግብር እያካሄደ ነው፡፡
ክፍለ ከተማው በገንዘብ ከ 63 ነጥብ 4 እንዲሁም በአይነት ከ26 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አሰባስቦ ነው ዛሬ የሚያስረክበው፡፡
የአይነት ድጋፉ 142 ሰንጋዎች፣ 167 በጎችና የተለያዩ የምግብ እና የመድኃኒት ግብአቶችን ያካተተ ነው።
ከክፍለ ከተማው የተውጣጡ ወጣቶች፣ የቀድሞ ሠራዊት አባላት እና አመራሮች ወደ ግንባር ሽኝት እንደሚደረግላቸውም ታውቋል፡፡
በድጋፍ ርክክብ መርሃ ግብሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በቆንጂት ዘውዴ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.