Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ወረርሽኝ የተቀዛቀዘው የቱሪዝም ዘርፍ እንዲያንሰራራ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ ዳግም አንሰራርቶ ምጣኔ ሃብታዊ ጠቀሜታውን ለማሳደግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተመለከተ።

“ቱሪዝም ለሁለንተናዊ ዕድገት” መሪ ሃሳብ የአለም የቱሪዝም ቀን ዛሬ በድሬዳዋ በፅዳት፣ በችግኝ ተከላና  በብስክሌት ውድድር  ተከብሯል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ ንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሃር፥የኮሮና ወረርሽኝ ከፍተኛ ጫና ከፈጠረባቸው ዘርፎች አንዱ ቱሪዝምመሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጫናውን በመቋቋም ዘርፉን ለማሳደግና ምጣኔ ሃብታዊ ጠቀሜታውን ትርጉም ባለው መንገድ ለመለወጥ በዘርፉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም አካላት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የኮሮና መከላከያ ፕሮቶኮልን በመጠበቅ ዘርፉን ለማሳደግና በየደረጃው የሚገኘውን ህብረተሰብ ንቃተህሊና በማሳደግ የሚገኘውን ጥቅም ትርጉም ባለው መንገድ መለወጥ ይገባልም ብለዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙራድ በደዊ በበኩላቸው፤ የኮሮና ወረርሸኝ የቱሪስት መዳረሻዎችና

የቱሪስት መዝናኛዎችን በመዝጋትና የዘርፉን ጥቅም በማሳጣት ተጽዕኖ ፈጥሮ መቆየቱን አውስተዋል፡ አሁን ግን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ዘርፉን ወደነበረበት ለመመለስ የተቀናጀ ጥረት  እየተደረገ  ነው ብለዋል፡፡

በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ክብሮምታደለ እንዳሉት፤ዘንድሮ በሃዋሳ ከመስከረም 8 ጀምሮ መከበር የሚጀምረው የዓለም የቱሪዝም ቀን በዘርፉ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.