Fana: At a Speed of Life!

ዓለም በቀጣይ ሊከሰት ለሚችል ወረርሽኝ በተሻለ መልኩ መዘጋጀት አለባት- ዶ/ር ቴድሮስ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለማችን በቀጣይ ሊከሰት ለሚችል ወረሽኝ ራሷን ማዘጋጀት እንደሚጠበቅባት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አሳሰቡ።

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በትናንትናው እለት ሀገራት በህብረተሰብ ጤና ላይ ትኩረት በማድረግ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በጠየቁበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት።

በአውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር በታህሳስ ወር 2019 በዓለማችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይናዋ ውሃን ግዛት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ እስካሁን በዓለም ዙሪያ ከ27 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ይዟል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህም እስካሁን 888 ሺህ 326 ሰዎች ህይወት ማለፉንም መረጃዎች ያመለክታሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፥ አሁን ላይ በዓለማችን ላይ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የመጨረሻው ወረርሽኝ አይደለም ብለዋል።

“ከታሪክ መማር እንደቻልነው የወረርሽኞች መከሰት በሰው ኑሮ ውስጥ ያለ ሀቅ ነው” ያሉት ዶክተር ቴድሮስ፥ “ስለዚህም ዓለማችን በቀጣይ ሊከሰት ለሚችል ወረርሽኝ ራሷን ከዚህ ቀደሙ በተሻለ መልኩ መዘጋጀት አለባት” ሲሉም አሳስበዋል።

ምንጭ፦ reuters.com

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.