Fana: At a Speed of Life!

የሊቢያ ተቃናቃኝ ሃይሎች የተኩስ አቁም ድርድር ያለስምምነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ ሞስኮ የተጀመረው  የሊቢያ ተቀናቃኝ ሃይሎች የተኩስ አቁም ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁ ተሰምቷል።

በሊቢያ ዓለም አቀፋዊ እውቅና ያለው የፋይዝ አል ሳራጅ አስተዳደር እና ተቀናቃኙ ጄኔራል ከሊፋ ሃፍታር በትናንትናው ዕለት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በሞስኮ ድርድር መጀመራቸው ይታወሳል ።

ይሁን እንጂ ተቃዋሚው ጄኔራል ከሊፋ ሃፍታር የተኩስ አቁም ስምምነቱን ሳይፈርሙ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ጄኔራል ሃፍታር የተኩስ አቁም ስምምነቱን ያልፈረሙትም ለድርድር የቀረበው ረቂቅ የጦራቸውን አብዛኛውን ፍላጎት ያላማከለ በመሆኑ ነው ተብሏል።

በሩሲያ እና ቱርክ አደራዳሪነት በሞስኮ ተጀምሮ የነበረው ይህ የተኩስ አቁም ስምምነት በሀገሪቱ  የተከሰተውን ቀዉስ ለማረጋጋት እንደሚያስችል ተስፋ ተጥሎበት ነበር።

የሀፍጣር ወታደሮች ትሪፖሊን ለመቆጣጣር ዓለም አቀፍ እውቅና ከተሰጠው መንግሥት ጋር የሚያደርጉትን ውጊያ እንደ አዲስ መጀመራቸው ተነግሯል።

ይህን ተከትሎም ዛሬ ጥት ላይ ትሪፖሊ ውስጥ ከባድ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱ ነው የተገለጸው።

ምንጭ ፦ www.rt.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.