Fana: At a Speed of Life!

የመስቃንና የማረቆ አካባቢዎችን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በጋራ እንነሳ ሲሉ አቶ ርስቱ ይርዳ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 7፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የመስቃንና የማረቆ አካባቢዎችን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ህዝቡ በጋራ እንዲነሳ የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳ ጥሪ አቀረቡ።
ርእሰ መስተዳዳሩ በኢንሴኖ ከተማ በተካሄደው የሁለቱ ህዝቦች ዕርቀ- ሰላም ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው በምስራቅ መስቃንና በማረቆ ወረዳዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት በዘለቄታው እንዲፈታ የሰሩ አካላትን አመስግነዋል፡፡
በአካባቢው የነበረው ሰቆቃና ስቃይ ተወግዶ አዲስ የሰላም አየር እንዲነፍስ ቱባ ባህሉንና የዳኝነት ስርአቱን በመጠቀም በይቅርታ መንፈስ ህዝቡ ዳግም ወደ ሰላማዊ ህይወቱ እንዲመለስ ላደረጉ የአገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
በአካባቢዎቹ የተከሰቱት አለመግባባቶች መሰረቱ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ለዘመናት ያሰረፀው መርዘኛ ሴራ ውጤት መሆኑን አመልክተው፥ ባህላዊ እሴቶች እንዲጠፉና እንዲዳከሙ እቅድ ነድፎ መስራቱንም አንስተዋል፡፡
በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው አካላት ችግሩ በይቅርታና በእርቅ እንዲፈታ በመስማማትና በጉዳታቸው ትውልድ እንዲድን ላደረጉት ትግልና ሰላምን ምርጫቸው በማድረጋቸውም አቶ ርስቱ አመስግነዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.