Fana: At a Speed of Life!

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 19 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በሱዳን ጉብኝት እያደረጉ ከሚገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ጋር ተወያዩ።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፖምፒዮ ጋር በሁለትዮሽ እና የተለያዩ የድጋፍ ጉዳዮች ዙሪያ ቀጥተኛ እና ግልጽ ውይይትን አድርገናል ብለዋል።
 
ከዚያም ባለፈ ሃገራቸው ከአሜሪካ ሽብርተኝነትን ከሚደግፉ ሀገራት ጥቁር መዝገብ የምትሰረዝበትን ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት።
 
ሱዳን የአልቃይዳው መሪ ኦሳማ ቢን ላደን በሀገሯ ከኖረበት ከ1990ዎቹ ጊዜ ጀምሮ ሽብርተኝነትን ከሚደገፉ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ ተካታ ቆይታለች።
 
ስለሆነም ሱዳን የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላትና ከዚህ ዝርዝር ላይ እንድትሰረዝ ትፈልጋለች ።
 
ለ30 አመታት ሱዳንን የመሩት ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል በሽር በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱም ነው የሚነገረው ።
 
ምንጭ፡-ቢቢሲ
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.