Fana: At a Speed of Life!

የባህር ዳር ነዋሪዎች ለዳውንት ግንባር ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ህዝብ ለታች ጋይንት – ዳውንት ግንባር ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ።

የከተማው አስተዳደር ከነዋሪና ከንግዱ ማህበረሰብ የሰበሰበውን የዓይነት ድጋፍ በተወከሉ የልዑካን አባላት አማካኝነት በታች ጋይንት – ዳውንት ግንባር አስረክበዋል።

የባህር ዳር ከተማ አፈ ጉባዔ አቶ ፍትሃነገስት በዛብህ ÷ የዓይነት ድጋፉን በታች ጋይንት ወረዳ አርብ ገበያ በመገኘት ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት÷ 10 ሚሊየን የሚገመት የምግብ፣ የአልባሳትና ግንባር ላይ ለሚገኘው ሃይል የሚውል የተለያዩ ዓይነቶች ድጋፍ ተደርጓል።

ድጋፉ ለሶስተኛ ዙር የተደረገ መሆኑን የገለፁት ደግሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊና የሎጂስቲክስ ዘርፍ አስተባባሪ ወይዘሮ ብርሃን ንጉሴ ሲሆኑ÷ የባህር ዳር ከተማ ህዝብ የጁንታው ግብዓተ መሬት እስከሚረጋገጥ ድረስ በየሳምንቱ ይህን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በመርሀግብሩ ላይ የንግድ ማህበረሰቡን ወክለው የተገኙት የባህር ዳር ከተማ ንግድ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ÷ በትግል ሜዳ የሚገኙ እህት ወንድሞቻችን እንዲቸገሩ አንፈልግም ስለሆነም ድጋፉን አጠናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት።

የባህር ዳር ነዋሪ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊና የሎጂስቲክስ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን ደጀኔ ÷ የህዝብ ደጀንነት ትግሉን በአሸናፊነት ለመወጣት ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የፎገራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወቀ በሬ ከህዝቡ የተሰበሰበውን የዓይነት ድጋፍ በቦታው በመገኘት ማስረከባቸውን ከአማራ ብልጽግና ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.