Fana: At a Speed of Life!

የነቀምቴ ከተማ ለችግረኛ ሕፃናትና ወጣቶች ከ200 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር የሴቶችና ሕፃናት ጽህፈት ቤት በተለያየ ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናትና ወጣቶች ከ200 ሺህ ብር የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
በዓለም ደረጃ ለ32ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም የሕፃናት ቀን ዛሬ በነቀምቴ ከተማ “በሕፃናት ላይ የሚደረግ ልማት የወደ ፊት የሀገር ልማት ነው” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ መስከረም ዓለማየሁ እንዳሉት፥ በዚሁ ጊዜ ከ200 ለሚበልጡ ሕፃናትና ወጣቶች ወደ 38 ኩንታል የሚጠጋ በቆሎ፣ ስንዴና ሩዝ እንዲሁም 70 ፍራሾች ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።
በትምህርታቸው የላቀ ውጤት አስዝግበው ከክፍላቸው ከ1አንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ለወጡ 20 ተማሪዎች ደግሞ የቦርሳ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የከተማው አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ባህሩ ኤባ በክብረ በዓሉ ላይ እንደተናገሩት፥ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ሕፃናትና ወጣቶችን በመርዳት ብቁ ዜጋ ማድረግ ይገባል።
የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር በ2014 የትምህርት ዘመን መጀመሪያ ለ7 ሺህ ያህል መሰል ተማሪዎች የትምህርት መሣሪያዎች ድጋፍ አድርጎ ትምህርት ቤት መላኩን ከኃላፊዋ ገለጻ ማወቅ መቻሉን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.